News News

ለህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጓተት ዋናው ምክንያት የብረት እና የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው መጠናቀቅ ከነበረበት እጅጉን በመዘግየቱ ነው ተባለ

ለህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መተጓተት ዋናው ምክንያት የብረት እና የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው መጠናቀቅ ከነበረበት እጅጉን በመዘግየቱ ነው ተባለ፡፡
ታህሳስ 25 ቀን 2011 .ም፤አምስተኛ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 16 መደበኛ ስብሰባው የህዳሴ ግድብና ናይል መሠረታዊ መረጃ እና የኮንስትራክሽን ሂደት አጭር ሪፖርት አድምጧል፡፡
ሪፖርቱ በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር / ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ቀረበ ሲሆኑ፤ አራት ዋና ዋና ነጥቦችን ይዟል፤የግድቡ የግንባታ ሂደትና ቴክኒክ ጉዳዮችን፣ግንባታውን በተመለከተ የሕዝብን ተሳትፎ ምን እንደሚመስል፣የህዳሴ ግድብ፤የናይል ትብብር ማቀፍ እና ከታችኛው ተፈሳስ አገሮች ጋር ያለው ግንኙነት ያለበት ሁኔታ እና በአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ምርትና አቅርቦት ያለበት ደረጃ የሚዳስሱ ናቸው፡፡
የህዳሴ ግድብ ሥራ በአገራችን ህዝቦችና መንግስት በከፍተኛ ርብርብ ግንባው እየተካሄደ ያለ ከመሆኑም ባለፈ በአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል መሆኑ፤ከሌሎች ፕሮጀክቶች በተለየ መልኩ በአገር ውስጥ ፋይናንስ ብቻ እየተሰራ ያለ፣ ህዝብን በሰፊው ያሳተፈና ለአለምም ጭምር መልካም ዓረአያ የሆነ ግድብ መሆኑን ክቡር / ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርቱ ገልፃዋል፡፡
ሆኖም የግድቡ መጓተት ዋንኛ ምክንያት በአገር ውስጥ አቅም ይሰራል ተብለው የተያዙት በምህድስና መስመር ሲታዩ በቀላሉ መሰራት የማይችሉ ብዙ ልምድ የሚጠይቁ ስራዎች ሆኖ ሳለ በመስኩ በጀማሪና ልምድ ለሌለው ለኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን መሰጠታቸው እና ከዚህ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ስራዎች መካሄድ ባለመቻላቸው መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ለኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ስራው የሚጠይቀው ዕውቀት ችሎታና ልምድ የሌለው በመሆኑ፣ፕሮጀክቱ ዝርዝር ዲዛይን ያልተሰራለትና መጀመሪያውኑ የእቅድ ችግር የነበረበት መሆኑ፣በግንባታው ወቅት ጥልቅ ሸለቆ ባማጋጠሙ የውሃ ጠለፋውንና የግድብ የመሠረት ስራው በሶስት ዓመት የተጓተተ እና ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የገባውን የስራ ግዴታ በተያዘለት ጊዜ አለመፈጸሙ ለፕሮጀክቱ መጓተት መንስኤ ናቸው ተብሏል፡፡
የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አሁን ያለበት ደረጃ የሲቪል ስራዎች 82 በመቶ፣ የኤሌኬትሮ መካኒካልና የብረታ ብረት ስራዎች አፈጻጸም 23 በመቶ የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም እስከ አሁን በአማካኝ 65 በመቶ መድረሱን ክቡር / ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ገልጸዋል፡፡
እነዚህን ችግሮች በመፍታት የተጓተቱ የፕሮጀክቱን ስራዎች በተቻለ ፍጥነት ለማጠናቀቅ መንግስት በአሁኑ ወቅት ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የነበሩትን ውሎች በማቋረጥ ለኢትዮጵያ ኤሌኬትሪክ ኃይል ቀድሞ ብረታ ብረትና እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እንደንኡስ ኮንትራት ይዞ ያሰሩ የነበሩትን ኮንትራክተሮች ሙሉ ኃላፊነት ወስደው እንዲሰሩ እና የኮንትራት ማሻሻያ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ውል ያልተፈረሙ ስራዎች በውስን ጨረታ የግዥ ሂደት ላይ መሆናቸውንና አንዳዶቹ ተጠናቀው ለውሳኔ መቅረባቸው ታውቋል፡፡ 
ግድቡ ለማጠናቀቅ በቅድሚያ ሊሰሩ የሚገቡ ወሳኝ ስራዎች መኖራቸውን የተጠቀሰ ሲሆን የግድቡን ውሃ ማስፈተሸ፣ወንዝ አቅጣጫ ማስቀየሪያ እና የሁለት ተርባይኖች የውሃ ማስተላለፊያ አሸንዳዎችና መቆጣጠሪያ በሮች እና የተረባይንና ጄኔሬተር ተከላ ከነተጓዳኝ ስራዎቹ መጠናቀቅ እንዳለባቸው ተገልጿል፤ 
በህዝብ ተሳትፎ በኩል አንዱና ዋነኛው ጉዳይ የፋይናስ አስተዋጽኦ ሲሆን ለግድቡ የሚሆነው ዋና ፋይናንስ ከመንግስት የሚመደብው እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቦንድ ሽያጭ የሚያቀርበው ሲሆን ሌላው ሕዝባችን በቦንድ ግዥ የሚቆጥበውና በስጦታ የሚሰጠው መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደ ሀገር የተጀመረው የታላቁ የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ በጠንካራ ሞራል በመነሳት ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠይቋል፡፡
ፕሮጀክቱን በሁለት ዓመት ለመጨረስ አስፈላጊው የማፋጠን ስራዎች ታቅደው እንዲተገበሩ እየተሰራ ሲሆን፤ በታህሳስ 2013 . ማመንጨት ታቅዶ አስፈላጊውን ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ነው የተባለው፡፡ ሙሉ ግዱቡም በታህሳስ 2015 . ይጠናቀቃል ተብሎ መታቀዱ ታውቋል፡፡
በቀረበው ሪፖርት ላይ ከም/ቤቱ አባላት በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፤ዶ/ ስለሺ በቀለ እና የህዳሴ ግድብ የሕዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ /ቤት ሃላፊ / ሮማን /ሥላሴ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ሮማን /ሥላሴ ማስተባበሪያ /ቤቱ የፕሮጀክት ግንባታ ክፍያን የሚመለከቱ ጉዳዮች እዳልሆነ እና የተሰጠው ኃፊነት ለግድቡ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሕዝብን ቅናቄና መፈጠር ነው ብለዋል፡፡ እስከ አሁን ድረስም የተለያዩ ዘዴዎችን ሲጠቀም መቆየቱን ለም/ቤቱ አብራርተዋል፡፡
በአሁን ወቅት የሕዝብ አመኔታ ዝቅ ያለበት ጊዜ በመሆኑ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችሉ የተለያዩ መድረኮችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ የገለፁ ሲሆን፤ ነገር ግን ሥራው ለጽ/ቤቱ ብቻ የሚተው እንዳልሆነ እና /ቤቱ ሊያግዝ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ዶ/ ኢኒጅነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው፤ የቴክኒክና የፋይናንስ ጉዳይ ፕሮጀክቱ /ቤቱን የሚመለከት ሲሆን፤ሙያተኞችን ናፓናሊሲቶችን ማሰባሰብ፣የተለያዩ ሪፖርቶችን መቀበል / /ቤቱን የሚመለከቱ እንደነበሩ አስታውቀው ሆኖም ፕሮጀክቱ ያጋጠሙትን ችግሮች ለመፍታት ከቀድሞ // ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸውን እና የፕሮጀክቱን ችግር ለመረዳትም 1 ዓመት በላይ መፍጀቱን ተናግረዋል፡፡
የግድቡን ግንባታ ሂደት የሚመለከቱ ሪፖርቶች በሚስጥር ተይዘው የሚቆይበት አካሄድ መኖሩን ያነሱት / ኢኒጅነር ስለሺ በቀለ፤ ከአሁን ወዲህ እንዲህ ዓይነቱ አሰራር እንደማይኖር እና ማንኛውም የፕሮጀክቱን የሚመለከቱ ጉዳዮች በግልጽ ይፋ ይደረጋሉ ነዉ ያሉት በንግግራቸው ፤የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 215 እንደሚጠናቀቅ የገለፁት / ኢኒጅነርን ስለሺ በቀለ ፕሮጀክቱ ህዝብ እንደተመኘው የሚቀር ሳይሆን ድህነትን ለመቅረፍ እውን ሚሆን ፕሮጀክት ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የደን ምንጣሮ እውቀት የሚጠይቅ ነው ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፤በአማራና ቤንሻንጉልጉሙዝ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶች እንዲይዙት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
ለህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጓተት ተጠያቂ የሆኑ ወንጀለኞች መጠየቅ እንዳለባቸውና ለተፈፀሙ ክፍተቶች ተጠያቂነት መረጋገጥ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
የህዳሴው ግድብናየግብጽ ፣ኢትዮጵያ፣ ሱዳን የሶስትዮሽ ውይይት እና የዲፕሎማሲ ሥራው ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው / ኢኒጅነር ስለሺ በቀለ ያረጋገጡት፡፡
ጉባኤውን ያጠቃለሉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው የግድቡን ስራዎች በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ ጠንካራ ክትትል የሚፈልግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የህዝብ ተሳትፎን በሚመለከት ሁሉም ኢትዮጵዊ እና ትውልደ ኢትዮጵዊ እስከ አሁን ድረስ ላደረጉት አስተዋፅኦ በምክር ቤቱ ስም ያላቸውን ትልቅና የላቅ አክብሮትና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም እንደ ሀገር ግድቡን ለማጠናቀቅ በሚደረገው ርብርብ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ያለብንን ችግር መፍታት አለብን ነው ያሉት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፤ የህዝብ ተሳትፎን ለማጠናከርና አመኔታን ለመፍጠር ጠንካራ ስራ መሰራት ይገባልም ነው ያሉት፡፡
የግድቡ ግንባት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ከታችኛው የናይል ተፋሰስ አገራት ጋር የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀሩ የስምምነት ነጥቦች ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሶስትዮሽ ድርድሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
በዚሁ ጉባኤ ምክር ቤቱ 4 ዓመት የስራ ዘመን 15 መደበኛ ቃለ ጉባኤውን መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አፅድቆታል፡፡