News News

የተጠሪ ተቋማት ምዘና ውጤት ተኮር እንሚሆን ተገለጸ፡፡

በተጠሪ ተቋማት ላይ የሚደረገው የአፈጻጸም ምዘና ከሂደት ባለፈ በውጤትና በተጠያቂነት ላይ እንደሚያተኩር  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፣

ቋሚ ኮሚቴው በሴቶች፣ህጻናት አና ወጣቶች ላይ የሚደርሰውን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ የሚገጥመኗቸውን ተግዳሮቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል  ውይይት አድርጓል፡፡   

በውይይቱም የ2011 በጀት ዓመት የ1ኛ የሩብ ዓመት አፈጻጸም እና በቀጣይ መቶ ቀናት ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት የቀረቡ ሲሆን በሩብ አመቱ ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የሚኒስቴር መስሪያቤቱ አወቃቀር አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የፈተለገውን ውጤት ማስበዝገብ እንዳልተቻለ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒሰቴር የእቅድ፣ክትትል ግምገማ ዳሬክተር የሆኑት አቶ ደሳለኝ የሱፍ ከ10 ያለነሱ ቁልፍ ተግባራትን በመጥቀስ የቀጣይ መቶ ቀናት እቅድ የሴቶች፣የህጻናትንና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያሉባቸውን ችግሮች በመቅረፍ  ውጤቶችን ለማስመዝገብ ስራዎችን በቁርጠኝነት ለማከናወን የሚስችሉ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተነሱት ግጭቶችና መፈናቀል ቅድሚያ የችግሩ ገፈት ቀማሽ  ተጎጂዎች ሴቶችና ህጻናት ስለሆኑ በሚደረገው ድጋፍ የበለጠ ትኩረት እየተሰጠ መሆኑን የገለጹት የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ያለም ግርማይ ችግሩን ለመቅረፍ ሁለቱን የከተማ ከአስተዳደሮች ጨምሮ ከክልሎች ጋር ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት እንደታቀደ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም በተለያዩ ምክንያቶች ጎዳና ላይ የሚገኙትን ህጻናት በማንሳት እና የሚደርስባቸውን የጉልበት ብዝበዛ በማስቀረት እንዲሁም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት በሚደረገው ርብርብ ከሚመለከከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት እንቅስተቃሴው መጀመሩን አስረድተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ የመቶ ቀን እቅዱ ዝርዝር ጉዳዮችን አካቶ የሚይዝ አንድ ቁልፍ ተግባር ሊኖረው እንደሚገባ ገልጾ በተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች ውጤት እየተለካ መሄድ እንዳለበት እና ማህበረሰቡ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስቧል፡፡

በተመሳሳይም የወጣቶች የስብእና ማዕከላት ግንባታ፣የኢኮኖሚ ጥያቄ እና የብድር አሰጣጥ ስርዓቱ ማነቆዎች ያሉበት በመሆኑ በቀጣይ ሚኒሰስቴር መስሪያ ቤቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴው አበባላት አሳስበዋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶ፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጎዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ በበኩላቸው ዘንድሮ በተቋማት ላይ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል በመስክ ምልከታ እና በእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚሆን ገልጸው ምዘናው ከሂደት ባለፈ  በውጤትና በተጠያቂነት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን አስረድተዋል፡

አያይዘውም በምዘናው ወቅት የተቋማትን አፈጻጸም ከፍተኛ፣መካከለኛ እና ዝቅተኛ ብሎ በመለየት ይፋ የሚደረግ እንደሆነና ከፍተኛ አፈጻጸም ላሳዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ማበረታቻ ሽልማት የሚበረከት መሆኑን ገልጸዋል፡፡