News News

ምክር ቤቱ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን አባላት ለመመደብ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አጸደቀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር /18/2011 ዓ/ም በካሄደው ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባው የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን አባላት ለመመደብ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በዚህመሰረት፡-

 1. ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል……………. የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር
 2. ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ………………………..የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር
 3. ክቡር አቶ ኡመር ሃሰን………………………….የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር
 4. ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ……………….የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር
 5. ክቡር ዶ/ር አሚር አማን………………………የጤና ጥበቃ ሚኒስቴ ርሚኒስትር
 6. ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ……………………የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር
 7. ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ……………………..የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር
 8. ክቡር አ ጃንጥራ ርአባይ………………………የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር
 9. ክብርት ወ/ሮ ያለምጸጋዬ አስፋው…………...የሴቶች ፣ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
 10. ክቡር አቶ ተመስገን ቡርቃ………………………በጠቅላሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል በሚኒስትር ማዕረግ የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ
 11. ክብርት ወ/ሮ ኬሪያኢብራሂም……………....የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ
 12. ክቡር ዶ/ር አብርሃም ተከስተ………………..የትግራይ ብ/ክ/መንግስት ም/ርዕሰመስተዳድር
 13. ክቡር አቶ ላቀው አያሌው……………………..የአማራ ብ/ክ/መንግስት ም/ርዕሰመስተዳድር
 14. ክብርት  ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን…………………የኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ም/ርዕሰመስተዳድር
 15. ክቡር አቶ አደምፋራህ………………………የሶሚሌ ብ/ክ/ክ መንግሰት ም/ርዕሰመስተዳድር
 16. ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ…………………….የሐረሪ ብ/ክ/መንግስት ርዕሰመስተዳድር
 17. ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር…………………..የደ/ብ/ብ/ህ/ መንግሰት ም/ርዕሰመስተዳድር
 18. ክቡር አቶ አብደላ አህመድ ሙሃመድ…..የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር ም/ከንቲባ
 19. ክቡር አቶ አበራ ባዬታ………………………..የቤንሻንጉልጉሙዝ ብ/ክ/መንግስት ም/ርዕሰመስተዳድር
 20. ክቡር አቶ ታንኳይ ጆክን……………………የጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰመስተዳድር

                     

በ2011 ዓ.ም. ለሚከናወነው አገር አቀፍ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን አማካሪ ካውንስል ሆነው ከተመረጡ በኋላ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡

አገሪቱ ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ለማከናወን የታሰበውን የህዝብ ቆጠራ ስራ ሊያደናቅፈው አይችልም ወይ የሚል ጥያቄ ከምክር ቤት አባል የተነሳ ሲሆን፣ መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን እንደሚሰራና ስጋት ሊሆን እንደማይችል የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጫላ ለሚ ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጂ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡

በአገራችን የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ ሰራዊቱ አገራዊ ተልዕኮውን በተሻለ ብቃት እንዲወጣ ለማድርግና አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎችን ለመደገፍ እንዲቻል ከ ሃስምንት በላይ የአዋጁ አንቀጾች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጫላ ለሚ አብራርተዋል፡፡

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን በጥልቀት ከተመለከተና ከተወያየበት በኋላ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝር ዝር እይታ መርቶታል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስትና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለልማት ፖሊሲ ፋይናንስ ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበለት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡

ብድሩ የተጀመረውን ልማት በፋይናንስ ለመደገፍ እንዲቻል ፣ የአገሪቷን የኢንቨስትመንት ተመራጭነት ለማሳደግ የሚረዱ እርምጃዎችን ለማገዝ እንዲሁም በግልጸኝነትና ተጠያቂነት ዙሪያ በመካሄድ ላይ ለሚገኙ የሪፎርም ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን የተከበሩ አቶ ጫላ ለሚ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረት ከአለም ባንክ የተገኘው የ 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ብድር ከወለድ ነጻ ሆኖ የስድስት አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ 38 አመታት ተከፍሎ የሚያልቅ መሆኑን አቶ ጫላ ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱም ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለ ገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡