News News

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከተለያዩ የዴሞክራሲ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በመወያየት የተጀመረው ሃገራዊ ለውጥ በተለመደው የአሰራር አካሄድ እንደማይሳካ ገለጹ፡፡

የምክር  ቤቱ  አፈ ጉባኤ  ከተለያዩ  የዴሞክራሲ  ተቋማት  ኃላፊዎች ጋር  በመወያየት  የተጀመረው  ሃገራዊ  ለውጥ በተለመደው የአሰራር አካሄድ እንደማይሳካ ገለጹ፡፡

ከህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር ከህዝብ  እንባጠባቂ ተቋም፣ ከሰብአዊ መብትኮሚሽን፣ ከፌደራልዋናኦዲተር፣ ከምርጫቦርድ እና ከስነ-ምግባርናፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተቋማት ጋር የትውውቅ ቆይታ አድርገዋል፡፡

የየተቋማቱ አመራሮች በነበራቸው የትውውቅ መርሃግብር በየተቋማቸው የተከናወኑ አፈጻጸሞችን፣ የቀጣይየ ትኩረት አቅጣጫዎችና ውስንነቶች ዙሪያ ከአፈ-ጉባኤው ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ተቋማቱ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ተጠያቂነትን ማዕከል ያደረገ ስራ እንደሚሰሩገልጸው፤   አመራሮቹ አመርቂ ውጤት ለማምጣት እንዲቻል ለውጤታማነቱ ምክርቤቱ ክትትልና ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አስተያየት አቅርበዋል፡፡

የህዝብ  ተወካዮች  ምክርቤት  አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው የተጀመረውን ሃገራዊ ለውጥ በተለመደው አሰራርና  አካሄድ መምራት  እንደማይቻል  አጽእኖት ሰጥተው ያብራሩ ሲሆን  “በተለመደው መንገድ ሰርቶ አዲስ የተለየ ውጤት መጠበቅ የለብንም” ያሉ ሲሆን፤ ለውጡን በሚፈለገው ደረጃ ለማስቀጠል በፍትህና በሰብአዊ  መብት እንዲሁም በግልጸኝነትና በተጠያቂነት ስርዓት ግንባታ በኩል አንገብጋቢ የሆነውን የህዝብ ጥያቄ ለመፍታት ሁሉም ተቋማት ከተለመደው ጊዜ በተለየ ተነሳሽነት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተቋማቱ ተግባራት እንደስማቸው ያማሩ እንዲሆኑ አፈ-ጉባኤው ጠቅሰዋል፡፡

ተቋማቱ ያሉባቸውን ሁለንተናዊ ችግሮች ለመፍታት በጋራ እንደሚሰሩ አብራርተው፤ ስራቸውን ሲያከናውኑ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ በተገቢ መንገድ ተደራሽ በማድረግ ህዝቡን ያማከለ ስራ መሰራት እንደሚኖርባቸውም ተናግረዋል፡፡