Participate

የኢትዮጵያ ፌዳራሊዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ መንግስት የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ

የኢትዮጵያ ፌዳራሊዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ መንግስት የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ  


የመሬት መራቆትና የተፈጥሮ ሃብት መመናመን የአገራችን ዋነኛ ችግር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የተፋሰስ ልማት ሥራ ይህን ችግር ለመቅረፍ ዓይነተኛ መፍትሄ እንደሆነ በመታመኑ የተፋሰስ ልማት ሥራ በአገራችን ለበረካታ ዓመታት ሲከናወን ቆይቷል፤ አሁንም በመከናወን ላይ ነወ፡፡ የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን ማስፋፋትና ማጠናከር ግብን ለማሳካት ከተከናወኑት ዋና ዋና ተግባራት መካከል ህብረተሰቡን ያሳተፈ  የተቀናጀ የማህበረሰብ  ተፋሰስ ልማት ዕቅድ በማዘጋጀት የተጐዱ መሬቶችን በመከለል መልሰው እንዲያገግሙ ማድረግ፣ በማሳና በወል መጠቀሚያ መሬቶች ላይ የተለያዩ የሥነ-አካላዊ (ፊዚካል) እና የሥነ-ህይወታዊ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች መስራት እና የተለያዩ የውሃ አማራጮችን መሰረት በማድረግ ውሃ የማሰሰባሰብ ሥራዎች በአበይትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በተፋሰስ ላይ የሚከነወኑ ሥራዎች የአፈር ለምነትን በማስጠበቅ ለምርትና ምርታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ እና የህብረተሰቡን ብሎም የአካባቢውን ለዓየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት በመቀነስና ተፅዕኖውን የሚቋቋምበትን አቅም በማሳደግ በኩል የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ታይቷል፡፡ ይህም አገሪቱ የነደፈችውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ስትራቴጂ ተግባራዊነት እውን በማድረግ በአገሪቱ ውስጥ ሙቀት አማቂ ጋዞችን ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ ቀዳሚ ስፍራ የሚይዘው የግብርና ሴክተር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን ለበርካታ ዓመታት በከፍተኛ የገንዘብና የጉልበት ወጭ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ቢቆዩም የአካባቢውን ማህበረሰብ ባለቤት በማድረግና የተጠያቂነት አሠራርን በማስፈን ዘላቂነታቸውን በማረጋገጥ በኩል በበርካታ አካባቢዎች ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ የማህበረሰብ ተፋሰሶች ልማት፣ አስተዳደርና አጠቃቀም በሕግ ማዕቀፍ ባለመታገዙም የልማቱ ቀጣይነትና የህዝብ ተጠቃሚነት በአሰተማማኝ ሁኔታ ተረጋግጧል ለማለት አይቻልም፡፡ እነዚህን የባለቤትነት፣ የተጠያቂነትና የዘላቂነት ችግሮች መቅረፍ የሚቻለው ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓትና ይህን የሚደግፍ የሕግ ማዕቀፍ ሲኖር ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት እንዲያስችል ታስቦ በሚኒስቴር መ/ቤታችን አነሳሽነት ይህ አዋጅ ሊረቀቅ ችሏል፡፡

Vote