Participate

የማዕድን ግብይትን ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ

የማዕድናት ግብይት ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ
 
. መግቢያ
ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ ማዕድን የሚመረትበትን አግባብ የሚወስን የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የማዕድን ኢንዱስትሪ እና የቴክኖሎጂ እድገት ሁኔታ ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ሕጉ በየጊዜውም እየተሻሻለ ሥራ ላይ እንዲውል ሲደርግ የቆየ ቢሆንም የማዕድናት ግብይትን አስመልክቶ ግን የከበሩ ማዕድንናት ግብይት አዋጅ ቁ. 651/2001 እሰከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የማዕድን ግብይት የሕግ ማዕቀፍ ያልነበረ ሲሆን ይህም አዋጅ ቢሆን የከበሩ ማዕድናትን ብቻ ማስተዳደር እንዲችል ተደርጎ የተዘጋጀ ነበር፡፡
በማዕድን ሥራዎች አዋጅ ቁጥር 678/2002 ድንጋጌ መሰረት በማዕድን ዓይነቱ ክፍል ተለይተው የተቀመጡት ማዕድናት ማለትም፤ የኮንስትራክሽን፣ የኢንዱስትሪ፣ ብረት ነክ፣ የከበሩና በከፊል የከበሩ ተብለው ባጠቃላይ 5 የማዕድናት ዓይነቶች እንዳሉ የተደነገገ ቢሆንም በነባሩ የግብይት አዋጅ ድንጋጌ እንዲተዳደሩ የተደረጉት የማዕድናት ዓይነቶች ግን የከበሩ ማዕድናት ብቻ በመሆናቸው ከነዚህ ውጭ የሆኑ ማዕድናትን በተመለከተ የግብይት ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር የሚቻልበት የሕግ ማዕቀፍ አልነበረም፡፡
በዋናነት አዋጁን በሌላ አዲስ አዋጅ እንዲተካ ለማድረግ የተፈለገው የግብይት ሕጉ የሁሉንም ማዕድናት ግብይትን አስመልክቶ ፈቃድ ወይም የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠትና ማስተዳደር እንዲያስችል ለማድረግ ሲሆን ነባሩ የግብይት ሕግ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ክፍተቶችን ለመሙላት፣ በፌዴራል እና በክልሎች ሊሰጡ የሚገባቸውን ፈቃዶችና የምስክር ወረቀቶችም ተለይተው እንዲታወቁና፣ የክልልና የፌዴራል ፈቃድ ሰጪ ባለሥልጣናት የየራሳቸውን ድረሻ በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡
ረቂቁም ከተዘጋጀ በኋላ ለሁሉም ክልሎች ረቂቁ እንዲደርሳቸው በማድረግ አንዲሁም የውይይት መድረክ በማዘጋጀት አስተያየታቸውን እንዲሰጡ የተደረገ ሲሆን የአማራ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የትግራይ ፣ የቤኒሻንጉል እና የጋምቤላ ክልሎች በጽሑፍና በስልክ በረቂቁ ላይ ያላቸውን አስተያየት ያቀረቡ በመሆኑ ከቀረበው አስተያየት ውስጥ በረቂቁ መካተት የሚገባቸው ሀሳቦች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ ረቂቁ ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተልኮ አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን በተሰጠውም አስተያየት መሰረት መስተካከል የሚገባቸው ሀሳቦቸ አንዲካተቱ በማድረግ የረቂቁ ሥራ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡ 
በመሆኑም የከበሩ ማዕድናት አዋጅ ቁጥር 651/2001 እንዲሻርና የሁሉንም ማዕድናት ግብይት ማስተዳደር በሚችል በአዲስ አዋጅ እንዲተካ ለማድረግ ረቂቁ እንዲፀድቅ ቀርቧል፡፡
 • . ነባሩን አዋጅ ቁጥር 651/2001 ለመለወጥና በሌላ አዋጅ መተካት ያስፈለገበት ምክንያቶች
አሁን በሥራ ላይ ያለው የከበሩ ማዕድናት ግብይት አዋጅ ቁጥር 651/2001 ለመጀመሪያ ጊዜ በ2001 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለ የማዕድናት ግብይት የሕግ ማዕቀፍ ሲሆን አዋጁ በተዘጋጀበት ወቅቱ ትኩረት የተሰጠው እና በአዋጁ የተካተተው በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራ የሚመረቱ የከበሩ ማዕድናት ግብይት ብቻ በመሆኑ በሀገራችን ከሚመረቱት የኮንስትራክሽን፣ የኢንዱስትሪ በከፊል የከበሩ እንዲሁም ከከበሩ ማዕድናት ውጪ ያሉት ብረት ነክ ማዕድናት ከዚህ ከግብይት የሕግ ማዕቀፍ ውጪ በመሆናቸው የሚቀርበውን የግብይት ጥያቄ ማስተናገድ የማይቻል ከመሆኑም በተጨማሪ ነባሩ አዋጅ የሚከተሉት ሁኔታዎች ምክንያት ሁሉንም ማዕድን ግብይት የማያስተናግድ ነበር፡፡
 • /   በባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ ከሚመረት ማዕድን ውጪ በአነስተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረት ሥራ ፈቃድ የሚመረቱ እንደ ታንታለም ያሉ ብረት ነክ ማዕድናትንም ሕጉ ሳይፈቅድ በዚሁ ሕግ በሚያዘው አሰራር ውስጥ እንዲያልፍ ሲደረግ የቆየ መሆኑ፤
 • /   አንዳንድ ፈቃድ የመስጠት ሥልጣንና ኃላፊነት ለምሳሌ የዕደ ጥበብ ሥራ ፈቃድ የመስጠትና የማስተዳደር ሥልጣን በአዋጁ ለፌዴራል መንግሥት ፈቃድ ሰጪ ባለሥልጣን ተሰቶት የነበረ ቢሆንም እነዚህ ባለፈቃዶች የሚገኙት በእያንዳንዱ የክልል ከተሞችና የተለያዩ ከተሞች ላይ በመሆኑ የፌዴራል ፈቃድ ሰጪ ባለሥልጣን ፈቃዱን መስጠትና ለማስተዳደር ከቦታዎች ርቀትና ከሥራው ብዛት አኳያ ሲታይ አመቺ ባለመሆኑ ሥራው በተግባር እየተሰራ ያለው በክልሎች ነው፡፡ በመሆኑም ሥራውን በውክልና ከመስጠት ይልቅ በተግባር ሲሰራ ለቆየውና በቀጣይም በቅርበት ሥራውን ማከናወን ለሚችል አካል በሕግ ሥልጣንና ኃላፊነቱን መስጠቱ አስፈላጊ በመሆኑ፤
 • /  በነባሩ አዋጅ በሚሰጠው ፈቃድ ለአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ብዙም ትኩረት ያልተሰጠበት መሆኑ በዚህ ረቂቅ ውስጥ ለአካባቢ ደኅንነት መሰራት የሚገባቸው ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማድረግ፤
 • / በነባሩ አዋጅ የከበሩ ማዕድናት የላኪነት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የወሰደ ሰው ያለገደብ ሁሉንም የከበሩ ማዕድናት ወደ ውጪ መላክ መቻሉ ሥራውን ያለገደብ ውስን ሰዎች ብቻ እንዲሰሩ የሚያደርግና ለሌላው ዜጋ የሥራ እድል የማይከፍት በመሆኑ በዚህኛው አዋጅ የሚሰጠው ፈቃድ እ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በማዕድን ዓይነቱ ተለይቶ እንዲሰጥ ለማድረግ፣
 • / በነባሩ አዋጅ የከልል እና የፌዴራል ፈቃድ ሰጪ አካላት ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር የመስጠትና የማስተዳደር ሥልጣንና ኃላፊነት ተለይቶ ያልተቀመጠ በመሆኑ በዚህኛው አዋጅ የፈቃድ ሰጪው ባለሥልጣን ሥልጣንና ኃላፊነት ተለይቶ እንዲቀመጥ ለማድርግ እንዲቻል፤
 • / በነባሩ አዋጅ ብሔራዊ ባንክ ወርቅና ብር መግዛት ጋር ተያይዞ የግብይት ሥርዓቱን ማበረታት ባለበት አግባብ ግልጽ ኃላፊነት አዋጁ ያለሰጠው መሆኑ ባንኩ በተለያዩ ጌዜያት በሚፈጽመውና በሚተዋቸው የማበረታቻ አሰጣጥ ሥርዓት በወርቅ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ሲፈጥር የነበረ በመሆኑ በዚህኛው አዋጅ ይህንን ሁኔታ እንዲካተት ለማድረግ እንዲቻል፤
 • / በነባሩ አዋጅ ከማዕድን ግብይት ጋር የተያያዙ ሕገወጥ ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎችን ያስተምራል ተብሎ የተቀመጠው ቅጣት በማዕድን ግብይት ላይ የሚደረገው ሕገወጥ ተግባር ከሚያስከትለው ጉዳት ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ አብዛኖች ሕገወጥ ተግባር ፈጻሚዎች አስተማሪ የሆነ ቅጣት እያገኙ አልነበረም በመሆኑም በዚህኛው አዋጅ አስተማሪ ሊሆን የሚችል ቅጣት እንዲቀመጥ ለማድረግ፤
 • /   በነባሩ የአዋጁ ድንጋጌዎች ላይ መለወጥ ወይም መሻሻል ያለባቸውና ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የማይሄዱ ተለያዩ ሀሳቦች በመኖራቸው፡፡
 • .   በነባሩ አዋጅ ድንጋጌ ያልነበሩና በዚህ ረቂቅ አዋጅ የተጨመሩ፣ የተሻሻሉ ወይም ከበፊቱ ለውጥ የተደረገባቸው ድንጋጌዎች
. የረቂቅ አዋጁ ይዘት
 • ረቂቅ አዋጅ ባጠቃላይ በ 4 ክፍሎች እና በ 38 አንቀጾች ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ሲሆን በቀደሞው አዋጅ ውስጥ ያልነበሩ ሀሳቦች የተካተቱበትን አንቀጾች በሚከተለው መልኩ ለማብራራት ተሞክሯል፤
. የረቂቅ አዋጁ ክፍል አንድ
 • 1 እስከ 4 በአጠቃላይ በ 4 አንቀጾች የአዋጁን ጠቅላላ ሀሳቦችን እንዲይዝ ተደርጎ አጭር ርዕስ፣ የቃላት ወይም ሀረጎች ትርጉም፣ የጾታ አገላለጽ፣ የተፈጻሚነት ወሰንና ዓላማን የሚገልጹ አንቀጾችን እንዲይዝ ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡
 • ክፍል በነባሩ አዋጅ ያልነበሩና አሁን በረቂቁ የተካተቱ፤
 • አንቀጽ 1 በነባሩ አዋጅ የከበሩ ማዕድናት ግብይት ይል የነበረው የአዋጁ አጭር ርዕስ በአሁኑ የማዕድናት ግብይት አዋጅ ተብሎ ሁሉንም የማዕድን ዓይነቶች ግብይት ማጠቃለል በሚችል መልኩ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡
 • አንቀጽ 2 በአዋጁ ትርጉም ክፍል ትርጉም ሊሰጣቸው የሚገባቸው በአዲስ መልኩ በአዋጁ የተካተቱትን አዳዲስ ሀሳቦችና የማዕድን ዓይነቶች እንዲተረጎሙ የተደረጉ ሲሆን ቀደም ሲል በነባሩ አዋጅ በ 16 ንዑስ አንቀጾች ተተርጉመው የነበረው በዚህ ረቂቅ 32 ያህል ቃላትና ሀረጎች ትርጉም እንዲሰጣቸው ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡ 
 • አንቀፅ 3 በቀድሞው አዋጅ የተፈጻሚነት ወሰኑ የከበሩ ማዕድናት ብቻ የሚመለከት ሲሆን በዚህኛው ረቂቅ ሁሉንም ዓይነት የማዕድን ምርት እንዲያጠቃልል ተደረጎ ተዘጋጅቷል፡፡
 • አንቀጽ 4 የአዋጁ ዓላማ የተገለፀበት አንቀጽ ሲሆን ይህ ክፍል በቀድሞው አዋጅ ያልነበረ በመሆኑ የአዋጁ ዓላማ በግልጽ መቀመጥ እንዳለበት ታምኖበት በአዲስ መልክ አሁን የተጨመረ አንቀጽ ነው፡፡
. ረቂቅ አዋጁ ክፍል ሁለት
 • ክፍል ሁለት ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ምዕራፍ 1 ስለፈቃድ አሰጣጥ፤ ምዕራፍ 2 ደግሞ ስለ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ የሚያወሱ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው፡፡
 • ክፍል በነባሩ አዋጅ ያልተካተቱና አሁን የተጨመሩ ሀሳቦች፤
 • ምዕራፍ አንድ
  • ምዕራፍ ስለፈቃድ የተደነገገበት ክፍል ሲሆን ከአንቀጽ 6 እስከ 20 ባጠቃላይ 15 አንቀጽ ያለው ክፍል ነው፡፡
 • አንቀጽ 6 ስለፈቃድ ዓይነቶች በተዘረዘረው ውስጥ በቀድሞው አዋጅ የአዘዋዋሪነት ፈቃድ የሚለው የፈቃድ ዓይነት ስያሜ በአጠቃቀም ላይ አስቸጋሪ ሆኖ የቆየ መሆኑ ስለታመነበት የአቅራቢነት ፈቃድ በሚለው እንዲተካ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም የማቅለጥ ፈቃድ የሚለው በቀድሞው አዋጅ ድንጋጌ ያልነበረ አሁን የተጨመረ ሲሆን ወርቅን ወይም ብርን ወይም ሌላ ብረት ነክ ማዕድን አቅልጠው ወጥ ቅርጽ የማስያዝ ሥራ ለሚሰሩ ሰዎች ሊሰጥ ይገባል ተብሎ የተጨመረ የፈቃድ ዓይነት ነው፡፡
 • አንቀጽ 7 በነባሩ አዋጅ የአዘዋዋሪነት ፈቃድ ይል የነበረውና በአሁኑ የአቅራቢነት ፈቃድ በሚለው የተተካው ፈቃድ ሲሆን ይህ ፈቃድ በየማዕድን ዓይነቱ ተለይቶ መሰጠት ያለበት መሆኑንና ለአንድ ዓይነት ማዕድን ፈቃድ የወሰደ ሰው የሁሉን ማዕድን ግብይት በዚያው በአንድ ፈቃድ መሥራት እንደሌለበት የተገለፀበት አንቀጽ ሲሆን የአንድ ማዕድን አቅራቢነት ፈቃድ የያዘ ሰው ምን መብት እንዳለው የተገለጸበት አንቀጽ ነው፡፡
 • አንቀጽ 8 ስለ ዕደ ጥበብ  ፈቃድ የሚያወሳ ሲሆን በቀድሞው አዋጅ ጠቅለል ባለ መልኩ የዕደ ጥበብ  ፈቃድ ተብሎ የተቀመጠ በመሆኑና በስሩ ሊኖሩ የሚቸሉት ሥራዎች ፈቃዶች በዚህኛው ረቂቅ ለይቶ ማስቀመጡ አስፈላጊ በመሆኑ በአሁኑ በማንጠር፣ በመቅረጽና በማጣመር ፈቃድ ተለያዩ ሆነው እንዲቀመጡ ተደርገዋል፡፡ በንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ተራ (ሐ) ላይ የተገለጸው የማጣመር ፈቃድ ቀደም ሲል ያልነበረ ሲሆን ብዙ ሰዎች በጌጥነት የተዘጋጀ ወርቅን ወይም ብር ከከበሩ ወይም በከፊል ከከበሩ ማዕድናት ከተሰሩ ጌጦች ጋር በማጣመር ሌላ ጌጥ በማዘጋጀት ለገቢያ በማቅረብ ላይ ቢሆኑም ፈቃድ ሳይኖራቸው ወይም ለማሳያ በማለት በከፍተኛ ዋጋ የሚሸጡበት ተጨባጭ ሁኔታ ያለ በመሆኑ ይህንን ለሚያዘጋጀት ሰዎች ፈቃድ በመስጠት መንግሥት ከማዕድን ንግዱ ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዲያገኝ ለማድረግ ታስቦ  እንዲጨመር የተደረገ ነው፡፡
 • አንቀጽ 10 ስለማዕድን ማቅለጥ ፈቃድ በነባሩ አዋጅ ያልነበረ ሲሆን በአዲስ መልክ የተጨመረ የፈቃድ ዓይነት ነው፡፡ ይህም ፈቃድ የሀገር ውስጥ ምርትን ወይም ከውጭ የሚገባ ብርት ነክ ማዕድናትን ከሌሎች ባለፈቃዶች ተረክቦ ለማቅለጥና ቅርጽ የማስያዝ ሥራ የሚሰራና የተፈለገውን ቅርጽ አስዮዞ የመመለስ መብት የሚሰጥ ሲሆን በሌሎች የግብይት ሥራዎች ላይ ባለዚህ ፈቃድ መሳተፍ እንደማይችል በሚገልጽ መልኩ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡
 • አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 2 ፊደል ተራ (ሐ) በነባሩ አዋጅ ለባህላዊ ማዕድን ማምረት ሥራ ባለፈቃድ እና ለሌሎች ለተወሰኑ ባለፈቃዶች የማዕድን አቅራቢነት (አዘዋዋሪነት) ፈቃድ ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአብዛኛው ያመረቱትን ማዕድን ከገዙት ጋር በመቀላቀል ላመረቱት ማዕድን ለመንግሥት መከፈል ያለበትን የሮያሊቲ ክፍያ የማይከፍሉበት ሁኔታና ከምርት የሚያገኙትን ገቢ የመሰወር ሁኔታ በተለይ በወርቅና በታንታለም አምራች አካባቢዎች ሲታይ የነበረ በመሆኑ የማዕድን ማምረት ባለፈቃድ የሆነ ሰው የማዕድን አቅራቢነት ፈቃድ ሊሰጠው እንደማይገባ በሚደነግግ መልኩ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡  
 • አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ተራ (መ) እና (ረ) የአቅራቢነት ባለፈቃድ የማዕድን ማከማቻ ቦታ እና ሥራውን የሚያከናውንበት ካፒታል መኖሩን ማሳየት እንደለበት አዲስ ሀሳብ የተጨመረ ሲሆን በንዑስ አንቀጽ 2 ላይም የዕደ ጥበብ ባለፈቃድ ለሚሰራው ሥራ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት እንዲያቀርብና ሥራውን የሚያከናውንበት ቦታ መኖሩን ማሳየት እንዳለበት የሚገልጽ ሀሳብ እንዲካተት ተደርጓል፡፡
 • በነባሩ አዋጅ ማዕድንን በጥሬው ስለመላክ እንጂ እሴት የተጨመረበት ማዕድን ስለመላክ ያላካተተ በመሆኑ በዚህኛው ረቂቅ አዋጅ አንቀፅ 12 እንዲካተት ተደርጓል፡፡
 • በነባሩ አዋጅ የላኪነት ፈቃድ ባለቤት ማዕድን ሲገዛና ሲሸጥ ሕጋዊ ደረሰኝ መጠቀምን በተመለከተ በግልፅ ያልተደነገገ በመሆኑ በዚህ ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 17 ንኡስ አንቀፅ 7 ፊደል ተራ (ሠ) ላይ ማዕድናት ሰገዛና ሲሸጥ በደረሰኝ መጠቀም እንዳለበት የሚገልጽ ሀሳብ እንዲጨመር ተደርጓል፡፡
 • አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 3 ነባሩ አዋጅ ፈቃድ በአንድ ዓመት መታደስ ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን በወቅቱ ያልታደሰ ፈቃድ በቅጣት እንደሌሎች የንግድ ፈቃዶች የሚታደሱበትን አግባብ ስላላስቀመጠ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ በቅጣት ፈቃድ መታደስ እንደሚኖር ተቀምጧል፡፡
 • አንቀጽ 17 ላይ በባለፈቃዶች ግዴታ ውስጥ የማዕድን ማከማቻ ቦታ አስፈላጊነት፣ ለንግዱ የሚያስፈልገው ወጪ መኖርን ማሳየትና የአካከባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት መሰራት ማስፈለጉን፣ እንዲሁም በንዑስ አንቀጽ 2 የተለያዩ ማዕድናት አቅራቢነት ፈቃድ ያለው ሰው እንደየ ማዕድን ዓይነቱ ለተጠቃሚ ወይም ማዕድን ለመግዛት ፈቃድ ላላቸው ሰዎች መሸጥ እንዳለበት እንዲሁም የገዛቸውንና የሸጣቸውን ማዕድናት መጠንና ዓይነት በየ3 ወሩ ለክልል ፈቃድ ሰጪ ባለሥልጣን ሪፖርት እንዲያቀርብ ተጨማሪ ሀሳቦች እንዲጨመሩ ተደርገዋል፡፡
 • ምዕራፍ ሁለት
  • ምዕራፍ ስለብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተደነገገበት ክፍል ሲሆን ከአንቀጽ 21 እስከ 27 በአጠቃላይ 7 አንቀጽ ያለው ክፍል ነው፡፡ በነባሩ አዋጅ ያልነበሩና አሁን በዚህኛው ረቂቂ እንዲካተቱ የተደረጉ ሀሳቦች፤ በነባሩ አዋጅ የከበሩ ማዕድናት ንግድ ላይ ብቻ ያተኩር ስለነበረ በዚህ ረቂቅ ግን ለማንኛዉም ማዕድን እንዲሆን የተደረገ ሲሆን ፍቃድ የሚሰጥም የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለተሰጠው የማዕድን አይነት እንደሚሆን በዚህ ክፍል ምዕራፍ አንድ ተደንግጓል፡፡
  • አዋጁ አንቀፅ 23 መሰረት የብቃት ማረጋገጫ ምሥክር ወረቀት ለማግኘት የሚቀርብ ማመልከቻ መያዝና መሟላት ስለሚገባው ጉዳይ ፈቃድ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች በረቂቅ አዋጁ ክፍል አንድ ምዕራፍ 1 አንቀፅ 13 የተደነገጉት እና ሌሎች ሚኒስቴሩ በመመርያ የሚወስናቸው መስፈርቶች እንደሚሆኑ ተደንግጓል፡፡  
. የረቂቅ አዋጁ ክፍል ሦስት
 • ክፍል አንቀጽ 28 ን ብቻ የያዘ አንቀጽ ሲሆን ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠትና ማስተዳደርን የሚመለከት በመሆኑ የፌዴራል መንግሥት እና የክልል መንግሥታት ስለ ማዕድናት ግብይት ፈቃድ ወይም የምስክር ወረቀት የመስጠትና የማስተዳደር ሥልጣንና ኃላፊነት እንዲቀመጥ የተደረገበት ክፍል ነው፡፡
 • አዋጅ ያልተካተቱና በዚህ ረቂቅ የተጨመሩ ሀሳቦች፣
 • የገበያ ማዕከል ማቋቋምን በተመለከተ በነባሩ አዋጅ ድንጋጌ ውስጥ ያልተካተተ ሲሆን በዚህ ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 28 ንዑስ አንቀጽ 2 ፊደል ተራ (ሐ) ላይ እንደየሁኔታው ለተወሰኑ ማዕድናት የገቢያ ማዕከል ማቋቋም እንዳለበት ተደንግጓል፡፡
 • በነባሩ አዋጅ ድንጋጌ ውስጥ ዋጋቸው በግልጽ የማይታወቁ ማዕድናትን ዋጋ መወሰን ያልተካተተ ሲሆን በዚህ ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 28 ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ተራ (መ) ላይ ሚኒስቴሩ ዋጋቸው በግልጽ የማይታወቁ ማዕድናትን ዋጋ መወሰን እንዲቻል እንዲሁም በፊደል ተራ (ሠ) ላይ ለገቢያ ደረጃቸው ተለይተው ለሚቀርቡ ማዕድናት ደረጃቸውን የመለየት ሥልጣን እንዲካተት ተደርጓል፡፡
 • በነባሩ አዋጅ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠትና የማስተዳደር ሥልጣንና ኃላፊነት ግልጽ በሆነ ሁኔታ ያልተደነገገ በመሆኑ በዚህ ረቂቅ አዋጅ አንቀጽ 28 ተለይቶ እንዲቀመጥ የተደረገ ሲሆን በቀድሞው አዋጅ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን የነበረውን የዕደ ጥበብ  ሥራ ፈቃድ፣ አዲስ የተጨመረው የማቅለጥ ፈቃድ እና የንግድ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመስጠትና የማስተዳደር ሥልጣንና ኃላፊነት በተጨማሪነት ለክልሎች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
. የረቂቅ አዋጁ ክፍል አራት
 • ክፍል ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን ከአንቀጽ 29 እስከ 38 ያሉትን ባጠቃላይ 10 አንቀጾችን የሚያጠቃልል ነው።
 • አዋጅ የልተካተቱና በዚህ ረቂቅ የተጨመሩ ሀሳቦች፣
 • አንቀጽ 29 ስለባንክ ሥልጣንና ኃላፊት የሚገልጽ ሲሆን፤
 • በንዑስ አንቀጽ 1 ባንኩ በባህላዊና በልዩ አነስተኛ ማዕድን ማምረት ባለፈቃዶች የሚመረቱትን የወርቅና የብር ማዕድን የመግዛት እንዳለበት ተደንግጓል ፣
 • በንዑስ አንቀጽ 3 ባንኩ ሊገዛቸው የሚችለውን ማዕድን አቅራቢዎችን ወይም የማዕድን አምራቾችን ሊያበረታታ የሚችል ክፍያዎችን ያመቻቻል የሚሉ ሀሳቦች ተጨምረዋል፡፡
 • አንቀጽ 31 ተረፈ ምርትን የሚመለከት ሲሆን በንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ዋጋ ሊያወጡ ስለሚችሉ ተረፈ ምርቶች መሸጥ ስለሚችሉበት ሁኔታ እንዲሁም ዋጋ የማያወጡ ተረፈ ምርቶች ደግሞ ስለሚወገዱበት አግባብ እንዲብራራ የተደረገበት አንቀጽ በተጨማሪነት እንዲካተት ተደርጓል፡፡
 • አንቀጽ 32 የግል መጠቀሚያን የሚመለከት ሲሆን በነባሩ አዋጅ ግለሰብ በጌጥነት ሊጠቀምበትና ይዞ መንቀሳቀስ የሚችለው የከበሩና የጌጤ ማዕድናት በተመለከተ በትርጉም ክፍል ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ ነበር፤ በዚህ ረቂቅ ግን በአንቀጽ 34 ስር እንዲደነገግ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም አንድ ግለሰብ በጌጥነት የሚጠቀምበትና ይዞት ሊንቀሳቀስ የሚችለውን ማዕድን መጠን በደንብ እንደሚወሰን ተደንግጓል፡፡፡፡
 • አንቀጽ 34 በነባሩ አዋጅ ሕግን በመጣስ ያለፈቃድ ማዕድናትን የሚያዘዋውሩ ወይም የማዕድናት ግብይት ሥራ ላይ የሚሳተፉ ወይም ከተፈቀደላቸው ግብይት ውጪ የማዕድን ግብይት ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሰዎች ማስተማሪያ እንዲሆን ተደንግጎ የነበረው ቅጣት ሲታይ በማዕድን ግብይት ጋር ተያይዞ ለፈፀም ከሚችለው የማጭበርበር፣ ሕገ ወጥ ያማዕድን ዝውውር እና የኮንትሮባንድ ሥራዎች አንጻር ሲታይ ሊያስተምር የሚችል አለመሆኑና አላቂ የተፈጥሮ ሀብት ላይ ሊፈፀም ከሚችለው የወንጀል ተግባር ጋር የማይጣጠም በመሆኑ በሁሉም ንዑስ አንቀጾች ላይ ከድርጊቱ ጎጂነት ጋር ሊጣጠም ይችላል የተባለ ከፍ ያለ የቅጣት መጠን እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡
  • . ማጠቃለያ
  • ነባሩ አዋጅ ውስጥ በነበረው ድንጋጌ ላይ በአዲስ መልክ የተጨመሩ፣ የተለወጡ፣ እንዲቀየሩ የተደረጉ እና መጠናቸው እንዲለውጥ የተደረጉ በርካታ ሀሳቦች ስለተካተቱ ነባሩን አዋጅ በማሻሻያ መልክ ከማዘጋጀት ይልቅ በአዲስ አዋጅ እንዲለወጥ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነ በዚሁ መሰረት የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በአዲስ መልኩ የተካተቱ ዋና ዋና ሀሳቦች ምን ምን እንደሆኑ ለማብራራት የተሞከረ ሲሆን ረቂቁ ካለው አስፈላጊነት ታይቶ እንዲጸድቅለን እንጠይቃለን፡፡  
Anonymousየማዕድናት ግብይት ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ
 
Vote