Participate

የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት ተቋጣጣሪባለሥልጣንን ለማቋቋም ስለተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ

 
የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት ተቋጣጣሪባለሥልጣንን
ለማቋቋም ስለተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ የቀረበ አጭር መግለጫ
 
1.መግቢያ
ነዳጅ ለማንኛውም ሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ የኃይል ምንጭ ነው፡፡ ሀገራችንም በየዓመቱ ከ2.8- 3.0 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ የነዳጅ ምርት (ቤንዚን፣ነጭ ናፍጣ፣ኬሮሲን፣ ቀላልና ከባድጥቁር ናፍጣ) እየገዛች ወደ ሀገር ውስጥ የምታስገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡በሀገራችን የነዳጅ ምርትካለው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የተነሣ የዋጋቁጥጥር የሚደረግበት በመሆኑየሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 23 ቀን 2001 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየወሩ እየተከለሰ ሥራ ላይ እንዲውል መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አነሳሽነት «ከመንግሥት ለመሠረታዊ ስትራተጂክ ሸቀጦች(ነዳጅን ጨምሮ) እየተሰጡ ያሉ ድጎማዎች፤ የበጀት እንድምታዎቻቸውና የወደፊት አቅጣጫ»በሚል ርዕ ጥስስብስስስ ጥናት (ህዳር/2011)እንዲዘጋጅ ተደርጐ በጥናቱ ከተለዩ ችግሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የነዳጅ የአቅርቦትና ሥርጭት የቁጥጥር ተግባር በተበታተነ መልኩ በተለያዩ ተቋማት የሚመራና ሕገወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ በተሟላ መልኩ የእርምት እርምጃ የሚወስድ አካል አለመኖሩ ነው፡፡ በመሆኑም የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭቱን በባለቤትነትና በተጠያቂነት የሚመራ፤ አፈጻፀሙን የሚከታተል፤ ድጋፍ የሚሰጥና የሕግ ጥሰትም ሲያጋጥም ተመጣጣኝ የእርምት እርምጃ የሚወስድ/የሚያስወስድ የቁጥጥርና የአሠራር ብቃቱ የተጠናከረ የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት ተቋጣጣሪ ባለሥልጣን ማቋቋም አሰፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
2. በአዋጁ ረቂቅ ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና ድንጋጌዎች
2.1ተጠሪነት
  • ተቋጣጣሪ ባለሥልጣንተጠሪነቱ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ለዚህም ምክንያቶቹ፡-
    • /  ነዳጅ ለሀገር ልማትና ብልጽግና ወሳኝ የኃይል ምንጭና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚወጣበት፣ የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግበትና በየወሩም ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ክለሣ እየተደረገበት ሥራ ላይ የሚውልና በዚሁ መሠረት ሚኒስቴርመስሪያ ቤቱ የዋጋ ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ዋጋ እያጠና ለመንግሥት የሚያቀርብ ሲፈቀድም ተግባራዊነታቸውን የሚከታተል መሆኑ፤
 
  • /  የአገር ውስጥ ንግድ እንዲስፋፋና ሕጋዊ አሰራር እንዲሰፍን ተገቢነት ያላቸውን እርምጃዎችን የሚወስድ፣ በክልሎች መካከል የሚደረጉ የንግድ ግንኙነቶችን የሚመራና የሚቆጣጠር መሆኑ፤
 
  • /    የአገሪቱን ሕጋዊ ስነ-ልክ ሥርዓት ለመተግበር እንዲቻል አስፈጻሚ አካላት የሚያስተባብር መሆኑ እና
 
  • /   አግባብ ባለቸው ሕጐች መሠረት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባሻገር የተሰጡ የንግድ ሥራ ፈቃዶች በተሰጠባቸው ዓላማዎች መዋላቸውን የሚቆጣጠር መሆኑ
  • ናቸው፡፡
 
  • የባለሥልጣኑሥልጣንናተግባር
የሚቋቋመው ተቋጣጣሪ ባለሥልጣንለተጠቃሚዎች የሚከፋፈሉነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች የሀገሪቱን ደረጃዎች እና መስፈርቶች ማሟላታቸውን፣ አቅርቦቱ አስተማማኝና ሥርጭቱ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን እና ለታለመለት አገልግሎት ብቻ መዋሉን የመቆጣጠር፣በነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭትሥራተሳታፊ የሆኑ ሰዎች በሕግ ወይም በውል ያለባቸውን ግዴታ በኃላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲወጡ የማስተባበር፣ የመደገፍና ለዚህም ተገቢውን የቁጥጥር ሥርዓት የመዘርጋት፣በነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት ጋር በተገናኘ ሕጋዊ ባልሆነ ተግባር ውስጥ በሚሳተፉ ወይም እንዲዓይነቱን ተግባር በሚፈፅሙ የግብይት ተሳታፊዎችላይ ተገቢውን የቅጣት እርምጃ በራሱ የመውሰድ/የማስወሰድ፣ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የነዳጅና የመጠባበቂያ ክምችት መጠን በዓይነት እንዲወሰንየማድርግ፣ የክምችት አስተዳደር ሥራ በሚገባ እንዲመራና የነዳጅ ማከማቻ ዲፖዎች እንዲገነቡ ድጋፍ የማድረግ፣የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች እንዲሁም የኢንዱስትሪያልና የትራንስፖርት ዘይትና ቅባቶችን የጅምላና የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የመጨረሻው የነዳጅ ተጠቃሚ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን እንድምታ በመገምገምእንዲሁም በነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት የሚሳተፉ ተቋሞችን የትርፍ ሕዳግ፣ የነዳጅ ማጓጓዣ የትራንስፖርት ታሪፍን እንደ ሁኔታው በማሻሻል የውሳኔ ሀሳብ ለሚኒስቴሩ እና ለገንዘብ ሚኒስቴር የማቅረብና ሲወሰንም ተፈፃሚነቱን የመከታተል እና የነዳጅንና የነዳጅ ውጤቶችን አቅርቦትና ሥርጭት በተመለከተ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ሥርዓቶችን የመቀየስ ሥልጣንና ኃላፊነት ተሰጥቷታል፡፡
3. ማጠቃለያ
  • አቅርቦትና ሥርጭት እንዲሁም ግብይት ተገቢነት ባለው የንግድ አሠራር መመራቱንና ለህብረተሰቡም ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ነዳጅ የማቅረብ የማከማቸት፣የማጓጓዝ፣ የማከፋፈልና የመቸርቸር ሥራ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ችግር እያጋጠመው የሚገኝ በመሆኑበዚህ ረገድ የሚታየውን ችግር ለመፍታት የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ግብይት ሕጋዊ ሥርዓትን ተከትሎ መከናወኑን የሚከታተልና የሕግ ጥሰትም ሲያጋጥም ተመጣጣኝ የእርምት እርምጃ የሚወስድ ተቋጣጣሪ ባለስልጣን ማቋቋም ወሳኝ ነው፡፡
 
  • የተዘጋጀው የአዋጅ ረቂቅ በዘርፉ የሚታየውን ችግር ይፈታል ተብሎ የሚታመን በመሆኑ ረቂቁ በምክርቤቱታይቶእንዲፀድቅይህአጭርመግለጫቀርቧል፡፡

 

Vote