News News

የኮሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው መስራት እንደሚፈልጉ በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ሊም ሁን ሚን ገለጹ

የኮሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው መስራት እንደሚፈልጉ በኢትዮጵያ የኮሪያ  አምባሳደር ሊም ሁን ሚን ገለጹ፡፡

የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ  የኮሪያን አምባሳደር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ፡፡     

በውይይታቸው ወቅት የኮሪያ ባለሃብቶች በሃገራችን የኢንቨስትመንት ዘርፍ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዙሪያ ተሰማርተው  መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኮሪያ ኢትዮጵያን  በትምህርቱ ዘርፍ ለመደገፍ ከሁለተኛ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ድረስ  ተማሪዎችን ተቀብላ እንደምታስተምርና ድጋፏንም አጠናክራ እንደምትቀጥል  አምባሳደር ሊም ሁን ሚን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያንና  የኮሪያን  የፓርላማ  ግንኙነት በማጠናከር ሁለንተናዊ የሆኑ ስራዎች እንደሚሰሩም የተከበሩ አቶ ታገሰ  ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያንና የኮሪያ የረዥም ጊዜ  ታሪካዊ  ትስስር አጠናክሮ ለማስቀጠል በባህልና  የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ መስራት እንደሚገባም ተወያይተዋል፡፡