News News

ፊንላንድ የሴቶችን የአቅም ውስንነት ለመቅረፍ በሴቶች አቅም ግንባታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራ ተገለፀ፡፡

ፊንላንድ የሴቶችን የአቅም ውስንነት ለመቅረፍ በሴቶች አቅም ግንባታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራ ተገለፀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ የፊንላንድን ልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሄሊና ኤራክሲነን ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ሴቶች፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና በአቅም ግንባታ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሺታዬ ምናለ ኢትዮጵያ ሁሉአቀፍ የሴቶችን ተሳትፎ ከምንጊዜውም በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት በትኩረት እየሰራች እንደምትገኝ ጠቅሰው፣ ተሳትፏቸውንና አቅማቸውን ለማጎልበት ምክርቤቱ በሴቶች ኮከስ አማካኝነት ከወረዳ እስከ ፌደራል ድረስ መዋቅር ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

አምባሳደር ሄሊና የኢትዮጵያና የፊላንድ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እ.ኤ.አ ከ1959 ጀምሮ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው፣ የሴቶችን የአቅም ውስንነት ለመቅረፍ በሴቶች አቅም ግንባታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ ሲሆን ለውጡን በተፈለገው መልኩ ለማስቀጠል መንግስት በፖለቲካው ዘርፍ ሴቶችን ሰፊው እያሳተፈ እንደሚገኝ ወ/ሮ ሽታዬ ለልዑካኑ ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሴቶችን ተሳትፎ አጠናክሮ ከማስቀጠል አኳያ እንደ ሃገር ውስንነት እንዳለ ተናግረው፣ ችግሩን ለመፍታት በሚዲያ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ወ/ሮ ሽታዬአክለውአብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ አባላት በሴቶች አቅም ግንባታ በኩል የሚስተዋሉትን ውስንነቶች ለመፍታት ከምክርቤቱ ጋር በጋራ እንደሚሰሩና የሃገራቸውን ተሞክሮ እንደሚያካፍሉ ተናግረዋል፡፡