News News

የገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለጸ፡

ምክር ቤቱ  ባካሄደው 25 መደበኛ ስብሰባው የገቢዎች ሚኒስቴርን 2011 በጀት ዓመት 6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል።

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን  2011 በጀት ዓመት 6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

 መስሪያ ቤቱ ባለፉት 6 ወራት 122 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 98.96 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ወ/ሮ አዳነች አብራርተዋል።

 የተሰበሰበው ገቢ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም  8.66 በመቶ እድገት ማሳየቱን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

 114.65 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ የግብርና ምርቶች፣ የከበሩ ማዕድናትና የውጭ ሃገር የገንዘብ ኖቶች መያዛቸውን ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል።

442 ቀጥታ ተሳታፊ ግለሰቦች (ኮንትሮባንዲስቶች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል።

በግማሽ አመቱ በተደረገው ኮንትሮባንድ የመከላከል ሂደት በድምሩ 509 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል፡፡

መስሪያ ቤቱ በአዲስ መደራጀቱንና በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስራ መስራት መቻሉን፣ በታክስ ማጭበርበር ስራ የተሰማሩ ሰዎችን በፍጥነት ወደ ህግ ማቅረብ መቻሉንና ታክስን የህዝብ አጀንዳ ማድረግ መቻሉን ምክር ቤቱ በጥንካሬ  ተመልክቶታል፡፡

በሌላ በኩል መስሪያ ቤቱ በርካታ ውስብስብ ችግሮች ቢኖሩበትም በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ ቀሪ ያልተከናዎኑ ገቢዎችን መሰብሰብ እንዳለበት የገቢዎች ፣በጀትና ፋይናንስ  ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ሰብሳቢ ወ/ሮ ለምለም ሃድጎ ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ ለማቋቋም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አጸደቀ፡፡

በዚህም መሰረት -

1. የህዝብ ተወካዮች /ቤት አፈ-ጉባኤ………………………ሰብሳቢ

2. የፌዴሬሽን /ቤት አፈ-ጉባኤ………………………………አባል

3. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት………………….አባል

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተወካይ…….አባል

5. የኢትዮጵያ ኢስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ ተወካይ………..አባል

6. የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ………………………………አባል

7. የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተወካይ…………………..አባል

8. የተከበሩ አቶ መሃመድ ቦልኮ…………………………………………..አባል

9. የተከበሩ / አድሃና ሃይሌ…………………………………………….አባል

10. የተከበሩ / በለጡ ኢድሪስ……………………………………….አባል

11. የተከበሩ / ተመስገን ባይሳ………………………………………አባል

12. የተከበሩ /ሮበቀለች ፈዬ…………………………………………አባል

13. የተከበሩ አቶ አለሙ ይመር………………………………………..አባል

14. የተከበሩ / አስካል ጥላሁን …………………………………አባል

በአባልነት የያዘው የውሳኔ ሃሳብ በምክር ቤቱ ጸድቋል፡፡

በሌላ ዜና ምክር ቤቱ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ተመልቶ  በዋናነት ለውጭ ግንኑነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ደግሞ ለንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮ ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ ከጥር 30/2011 እስከ የካቲት 30/2011/ ለአንድ ወር እረፍት እንደተዘጋ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ / ሽታዬ ምናለ አሳውቀዋል፡፡