News News

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው 9ኛ ልዩ ስብሰባው በ2012 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር ተወያዬ፣

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው 9ኛ ልዩ ስብሰባው በ2012 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር ተወያዬ፣

የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምና አዋጭነትን እና የመሰረተ ልማት አቅርቦትን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥተዋል፡፡

ፕሮጀክቶች የሚዘገዩበት ዋናው ምክንያት ከኮንትራክተሮችና ከአማካሪዎች አቅም ውስንነት ጋር ተያይዞ በሚያጋጥም የዲዛይንና የቅድመ ዝግጅት ችግር እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ ነባር ፕሮጀክቶች በ2012 በጀት አመት ቅድሚያ እንደተሰጣቸውና ከአዋጭነት አኳያ አዳዲስ ፕሮጀክቶች መካተታቸውንም አመላክተዋል፡፡

ከስራ እድል ፈጠራ አኳያ ድህነት ተኮር በሆኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ያሉት ሚኒስትሩ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋትና የግሉን ዘርፍ ማጠናከር ችግሩን ለማቃለል ስለሚያግዝ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በጀትን በቁጠባ ለመጠቀም እንዲቻል ለሁሉም አስፈጻሚ ተቋማት መመሪያ ቢተላለፍም አብዛኛዎቹ ተግባራዊ እያደረጉት ስላልሆነ በቀታይ ተከታትሎ መመሪያውን ለማድረግ ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ የኦዲት ግኝት ላይ በሚወሰደው ተከታታይ እርምጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡

የዋጋ ግሽበቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለውን የህብረተሰብ በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ በመሆኑ በቀጣይ የንግድ ሚዛኑን ለማስተካከል ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡

የመሰረተ-ልማት አቅርቦት በመንግስት ብቻ ሊሸፈን እንደማይችል ያመላከቱት ሚኒስትሩ በቀጣይ ለዘርፉ የምንፈጽመውን ብድር በማቆም በውጭ ኢነቨስትመንት መታገዝ የሚያስችለንን ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የብድር ጫናችን እንዲቀንስ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ እስካሁንም በተበደርነው ሃብት በኢኮኖሚ እድገት አመንጭ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥተን የሰራን በመሆኑ ማክሮ ኢኮኖሚውን ጫና ውስጥ የሚከት የብድር ጫና የለብንም ብለዋል፡፡