News News

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ከቱርኳ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የቱርክ አምባሳአደርን ያፕራክ አልፕን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ኢትዮጵያ እና ቱርክ የረጅም ጊዜ የድፕሎማሲ ግንኙነት እናዳላቸው የገለጹ ሲሆን በቀጣይም የሁለቱን አገሮች መልካም ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የቱርክ ኢንቨስትመንቶች እንዲስፋፉ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚደረግ የገለጹት አፈ-ጉባዔው በሌላ በኩል በተወሰኑ ኩባንያዎች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በትብብር ለመፍታት እንደሆነ ነው የውይይቱን አስፈላጊነት የተናገሩት፡፡

የቱርክ አምባሳድር ያፕራክ አልፕ በበኩላቸው ቱርክ በኢትዮጵያ በምታደርገው  ኢንቨስትመንት ለበርካቶች ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የፈጠረች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር 2017 460 በላይ ኢትዮያውያን ዜጎች የትምህርት እድል የሰጠች መሆኑን ገለጸው በቀጣይም የሁለለቱን አገርች ግንኙነት የበለጠ ለማጎልበት ጥረት እንደሚያደርጉ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ  ተናግረዋል፡፡    

በመጨረሻም በሁለቱ አገሮች መካከል ያሉትን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነቶች  ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የበለጠ ትኩረት ስጥተው እንደሚሰሩ ነው የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የገለጹት፡፡