News News

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ የሰርቪያ አምባሰደር በጽ/ቤታቸው ተቀብሎ አነጋገሩ

በኢትዮጵያና  ሰርቪያ  ያላውን የፓርላመንታዊ ሥርዓት ግንኙትን ማጠናከር  የሚያስችል ሥራ ለመስራት ከሰርቪያ አምባሰደር ጋር መስማማታቸውን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ አስታወቁ፡፡

ሚያዚያ 09 08/ 2011 ዓ.ም አፈ ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ በኢትዮጵያ የሰርቪያ አምባሳደርን አሌክስአንደር ሪስቲችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አናጋግረዋል፡፡

አፈጉባኤ አቶ ታገሠ ከአምባሳደር አሌክስአንደር ሪስቲች  ጋር በነበራቸው ቆይታ እስካሁን በሁለቱ አገራት መካከል ስለነበረው ግንኙነትና ስለ ቀጣይ የሁለቱ አገራት የግንኙነት ራዕይ ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል።

ከውይይቱ በኋላ አቶ ታገሠ  በሁለቱ ሃገራት መካከል በፓርላሚንታዊ ሥርዓት ያለውን ግንኙት ማጠናከር በዋናነት የሚሰራ መሆኑን ገልፀው፡ የሰርቪያ መንግስት በኢትዮጵያ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በከተማ ልማት ሥራዎች ድጋፍ ለማድረግ እንደሚፈልጉም ከውይይቱ በኃላ ተናግረዋል፡፡

የሰርቪያው አምባሳደር በበኩላቸው እንደገለጹት ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል የነበረውን  ታሪካዊ ግንኙነታቸውን እና ትብብራቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረው ግንኙት የቀድሞዋ ዮጐዝላቪያ  ከ6ዐ አመታት በፈት በኢትዮጵያ ኢምበሲዋን መክፈቱን አምባሳደሩ አስታውሰው፡ ከ15 አመታት በፊት በሃገሪቱ በተከሰተው ግጭት የቀድሞዋ ዩጐዝላቪያ  6 ሃገራት ሆና መከፋፈሏን አውስቷል፡፡

ለ6 ከተከፈሉት ሃገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሰርቪያ በኢትዮጲያ የዩጐዝላቪያ ኢንባሲን በመረከብ የነበረውን ግንኙት በማስቀጠል የተጠናከረ ግንኙነት መፍጠሩም በዚሁ ጊዜ ተጠቁሟል፡፡

የቀድሞዋ ዩጐዝላቪያ  የአሁኗ ሰርቪያ የፋሽስት ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ባደረገው ወረራ ከኢትዮጵያ ጐን በመቆም የማይረሳ ውለታ የፈፀመች ስትሆን፡ ለዚሁ መታሠሲያ የቆመውን የየካቲት 12 የሰምአታት መታሠቢያ ሃውልትን ጨምሮ በሌሎቹም የግንባታ ስራዎች ላይ ተሳትፏቸው የጎላ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡