News News

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 38ተኛ መደበኛ ስብሰባው የሰላም ሚኒስቴር የ2011 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ ሪፖርት አድምጧል

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 38ተኛ መደበኛ ስብሰባው የሰላም ሚኒስቴር የ2011 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ ሪፖርት አድምጧል፡፡

የአገራችን ፌዴራላዊ ስርዓት በተገቢው ተግባራዊ እንዳይሆን ወቅታዊ ፈተና እየሆነ ያለው በተዋረድ ያሉ የአመራሮች ፖለቲካ ቁርጠኝነት ማነስ ነው ተባለ፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በአገሪቱ አዲስ የተቋቋመ ተቋምና በበጀት ዓመቱ የመንግስት የሪፎርም አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ ለተጠሪ ተቋማት ድጋፍ በማድረግ  የአገሪቱን የጸጥታና የደህንነት ተቋማትን አቅምን በማሳደግ የህብረተሰቡን የሰላም ግንባታ ተግባራዊ በማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወትና ደህንነትን ለማረጋገጥ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

በማህበራዊ አቅሞችን መሰረት ያደረገ የሰላም ግንባታ አቅጣጫን በመከተል ከተለያዩ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ኡጋዞች፣ ሱልጣኖች፣ የኪነ-ጥበብ ቤተሰብ፣ ከእናቶችና ወጣጦች የተወጣጦ አካላት ጋር በመሆን ለለውጡ እንቅፋት እየሆነ ላለው ግጭቶችንና አለመረጋጋትን ለመግታት የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር የግንዛቤ የመፍጠር ብሎም ዜጎች ሚዛናዊ አስተሳሰብ ባሌበት እንዲሆኑ ከውጪም ሳይቀር በመጡ ባለሙያኞች ስልጠናዎች የመስጠት ስራ እንደተሰራም በሪፖርቱ ተቀምጧል፡፡

በወቅቱ ሪፖርቱን ያዳመጠው ም/ቤቱ ጥያቄዎችን ያነሳ ሲሆን አሁን ላይ በየአከባቢው የሚነሱ ግጭቶች በተገቢው በመፍታት የህግ የበላይነት በማረጋገጥ ተገቢውን ዕርምጃ ለመውሰድ ያልተቻለው ለምንድነው ሲል ተጠይቆ ከወረዳ እስከ ክልል ያሉ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ቁርጠኛ ባለመሆን በወቅቱ የተነሱ ግጭቶችን ለማስቀረትና ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት ካለመቻሉም በተጨማሪ ለሰላም መደፍረስ ተዋናይ የሆኑ አካላትም እንዳሉ የገለጹት ወ/ሮ ሙፈሪያት ወንጀለኞችን ለመያዝና ወደ ህግ እንዲቀርቡ ለማድረግ በተሰራው ስራ 2200 በላይ የሚሆኑት ግለሰቦችን መዝገባቸው በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትና 468 ተጠርጣሪዎችን ወደ ህግ የማቅረቡ ስራ ቢሰራም አፈጻጸሙ አሁንም 50 በመቶ ብቻ እንደሆነ ነው፡፡

ም/ቤቱ ለግጭቶች ቅርብ የሆኑና ስጋት ያለባቸውን አከባቢዎችን በመለየት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታ ከተለያዩ ዩኖቨርስቲዎች ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሆነ ከሚ/ሩ የተነሳው በቂ እነዳልሆነና በቀጣይም ሁሉን ዩኒቨርስቲዎችን በማሳተፍ በተለይ ከጭናቅሰን እስከ ሞያሌ፣ በጉራጌ ዞን ማረቆ ወረዳ እንዲሁም በጌዴኦ ዞን እና ጉጂ ጋር ያለውን ግጭት በጥናት በመለየት ቀጣይ በዘላቂነት ሰላምን በማረጋጥ የዜጎች ደህንነት ላይ መሰራት እንዳለበት ተነስቷል፡፡

ም/ቤቱም ለበርካታ ጊዜያት የቆዩ የማንነት፣ የወሰንና ሌሎች ጥያቄዎች በትንሽ ምክኒያቶች ሌላ መልክ እየያዘ ወደ ነፍስ መጥፋት፣ ንብረት መውደም እና በማፈናቀል ችግር እያደረሰ እንዲሁም በሌላ በኩል ህገ ወጥ የገንዘብ፣ የመሳሪያ፣ የሰው ዝውውርና ኮንትሮባንድ ንግድ ተመጋጋቢ በመሆን የሰላም ጠንቅ በመሆኑ ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ያለው በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተቀምጧል፡፡  

በውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴውም በቀጣይ ሚ/ር መ/ቤቱ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ያሏቸውን ለተፈናቀሉ ዜጎች ከአደጋ ስጋት ስራው ተደራሽነቱ ዝቅተኛ መሆኑ፣ ስደተኞችና ከስደት ተመላሾችን እንዲሁም ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ከማቋቋም ቀጣይ የዝናብ ጊዜ ሳይደርስ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ ረገድ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ መስራ እንዳለበት ነው፡፡

 በመጨረሻም  ቋሚ ኮሚቴው አመራሮች በህገ ወጥነት ተሳትፎ ብሎም የፖለቲካ ቁርጠኝነት በማነስ የህግ የበላይነት ለማስከበር ባልተቻሉ አከባቢዎች ላይ የሚሰራው ስራ በትኩረት ሊታይ እንደሚገባ በግብረ መልሱ ላይ አስቀምጧል፡፡