News News

ምክር ቤቱ ለኢኮኖሚ ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ድጋፍ ረቂቅ አዋጅ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ፡፡

ምክር ቤቱ ለኢኮኖሚ ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ድጋፍ ረቂቅ አዋጅ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵ እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለኢኮኖሚ ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈጸሚእንዲውል የተገኘውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአብጫ ድምጽ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ፡፡

ይህ የብድር ስምምነት ምክር ቤቱ ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ ለገቢዎች፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ቋሚ ኮሚቴው በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ከተወያየ በኋላ ከአስረጂዎች ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ሰፊ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ለምክር ቤቱ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ሪፖርቱን አስመልክቶ ምክር ቤቱ በብድር ስምምነቱ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱም አዋጁ በጥልቀት መታየት እንዳለበት በመጠቆም በ6 ተቃውሞ እና በ3 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ለሌላ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡

ምክር ቤቱ የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያና በእስራኤል መንግስት መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መንግስት መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

በእለቱም በኢትዮጵያ መንግስት እና በሞሮኮ ንጉሳዊ መንግስት መካከል የተደረገውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ኮሚቴው ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጅ 1105/2011 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡